የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ውጤት
ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 12ኛ
መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በሁሉም ባለአክሲዮኖች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው
ለምርጫ የቀረቡ እጩዎች ስም ዝርዝር እና ያገኙት የድምጽ ውጤት፡፡
Draft MOA of BIC
MOA of BIC
የቡና
ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር
የተሻሻለ
መመሥረቻ ጽሑፍ
የኩባንያው
ባለአክሲዮኖች ኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረጉት 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እ.ኤ.አ በ2004ዓ.ም በመሥራች አባላት የጸደቁትን
የማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ድንጋጌዎች በማሻሻልና በመመስረቻ ጽሑፉ ውስጥ በማጠቃለል በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ
አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 400(1) መሰረት ጸቅዶ በስራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ከመመስረቻ ጽሑፍ መጽደቅ በኋላ በማኅበሩ
የተደረጉ ለውጦችን በተለይም የተከፈለ ካፒታል መጠን ጭማሪን፤ ከካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሕግ ማዕቀፎች እና በአፈጻጸም የታዩ
ጉድለቶችን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
የኩባንያው
ባለአክሲዮኖች ታሕሳስ 16 ቀን 2018 ባደረጉት 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር
1243/2013 አንቀጽ 400(1) መሰረት የማኅበሩን መመስረቻ ጽሑፍ እንደሚከተለው አሻሽሎ አጽድቋል፡፡
አንቀጽ አንድ
የኩባንያው መጠሪያ
የኩባንያው
መጠሪያ ቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡
አንቀጽ ሁለት
የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤትና ቅርንጫፎች
2.1 የኩባንያው ዋና መ/ቤት በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ
ይሆናል፡፡ አድራሻውም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 06፣ የቤት ቁጥር 438/ለ፣ ስልክ ቁጥር 011-126 3460፣ ፋክስ ቁጥር
011-1119207፣E-mailAddress:info@bunnainsurance.com፡Website:www.bunnainsurance.com ነው፡፡
2.2 ኩባንያው በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች እና ከኢትዮጵያ ውጭም
ቅርንጫፎች እንዲቋቋሙ መወሰን ይችላል፡፡
አንቀጽ ሦስት
የባለአክሲዮኖች ስም፣ ዜግነት፣ የተፈረመና
የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት
3.1 የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስም፣ አድራሻ፣ዜግነት፣
የተፈረመና የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት ከዚህ መመስረቻ ጽሑፍ ጋር አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 715 የተዘረዘሩት
ናቸው፡፡
አንቀጽ አራት
የኩባንያው የሥራ መስክ እና ዓላማ
የኩባንያው የሥራ መስክና
ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
4.1 ማናቸውንም ዓይነት የጠቅላላ መድን ስራዎች እና የህይወት መድን
ስራን ማካሄድ፣
4.2 አክሲዮኖችን፣ ቦንዶችን፣ የዕዳ ሰነዶችን ማውጣት እና መዋዋል፣
4.3 በመድን ስራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 እና በማሻሻያ አዋጅ
ቁጥር 1163/2012 ድንጋጌዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች መሰረት የኩባንያውን የንግድ ዓላማዎች በሚያግዙ
እና በሚያጠናክሩ ተጓዳኝ በሆኑ ተግባራት ላይ መሳተፍ፡፡
አንቀጽ አምስት
የኩባንያው ካፒታል
የኩባንያው የተፈረመ እና የተከፈለ ካፒታል ብር 1,000,000,000 (አንድ ቢሊዮን ብር) ነው፡፡
አንቀጽ ስድስት
ስለአክሲዮኖች
6.1
ኩባንያው እያንዳንዳቸው ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ዋጋ ያላቸው በጠቅላላው 10,000,000 (አስር
ሚሊዮን) አክሲዮኖች ያለው ሲሆን፣ ሁሉም አክሲዮኖች እኩል ዋጋ ያላቸው፣አንድ ዓይነት እና ልዩ መብት የማያስገኙ ተራ አክሲዮኖች
ናቸው፡፡
6.2
የኩባንያው ካፒታል መጨመር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18፣ በኢፌዲሪ የንግድ ሕግ አንቀጽ
442 እና አግባብነት ባላቸው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሕጎች መሠረት ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡
6.3
አክሲዮኖች
የማይከፋፈሉ ናቸው፡፡ ሆኖም ብዙዎች ሰዎች የአክሲዮን የጋራ ባለሀብት በሚሆኑበት ጊዜ የሁሉንም ባለአክሲዮኖች መብት የሚወክል ከመካከላቸው
መወከል አለባቸው፡፡የጋራ ባለሀብቶች ከባለአክሲዮንነት ለሚመነጩ ግዴታዎች ሳይከፋፈል በአንድነትና በነጠላ ኃላፊዎች ናቸው፡፡
6.4
ኩባንያው ሁሉንም አክሲዮኖች የኢትዮጵያ
ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ግዑዝ አልባ በሆነ ኤሌክትሮኒክስ መንገድ ይይዛል፡፡
6.5
ኩባንያው በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሚያወጣቸው
እና ሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጐች
የሚወሰኑ
ዝርዝሮችን ያካተተ የባለአክሲዮኖችን መዝገብ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ አደራጅቶ ይይዛል፤ በማዕከላዊ የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ግምጃ ቤት ያስመዘግባል፤ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግምጃ
ቤት ጋር በመተባበር ወቅታዊ መረጃዎችን
ያዘምናል፡፡
6.6
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6(5) መሰረት የተደራጀው መዝገብ በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በመደበኛ
የሥራ ሰዓት ክፍት ሆኖ በባለአክሲኖችም ሆነ አግባብነት ያለው ሰው ያለ ክፍያ እንዲመለከተው
ይደረጋል፡፡
6.7
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6(5) ስር የተደራጀውን የመዝገቡን ግልባጭ ወይም በአጭሩ የተውጣጣ ጽሑፍ ባለአክሲዮን ወይም ሌላ አግባብነት ያለው ሰው እንዲሰጠው
ሲጠይቅ የተወሰነውን የአገልግሎት ክፍያ በመፈጸም ማግኘት ይችላል፡፡
6.8
የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት በኤሌክትሮኒክ
ዘዴ የሚካሄድበትን አግባብ አስመልክቶ በሌሎች ሕጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አክሲዮኑ በማዕከላዊ የሰነደ
ሙዓለ ንዋይ ግምጃ ቤት መመዝገብ አለበት፡፡
6.9
የዳይሬክተሮች ቦርድ በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተፈቀደውን የካፒታል ጭማሪ አግባብነት ያለውን ሕግና መመሪያ በመከተል
ፈቃድ ባላቸው ባለሙያዎች አስጠንቶ አክሲዮኖች ከተፃፈባቸው ዋጋ በሚበልጥ
ዋጋ እንዲወጡ እና ለሽያጭ የሚወጡበትን
ዋጋ ይወስናል፡፡
6.10
በኢንሹራንስ እና የካፒታል ገበያ ሕጐችና መመሪያዎች ወሰን ውስጥ እና በተገቢው የተቆጣጣሪ
ባለሥልጣን ፈቃድ እና መስፈርቶች መሠረት የተለያዩ ዓይነት ሠነደ ሙዓለ
ንዋይን ማለትም አክሲዮን፤ ቦንድ፤ተዛማጅ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ወይም እነዚህን የመሰሉ የተለያዩ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ማውጣትና ለሽያጭ ማቅረብ፤ መሸጥና መግዛት እንዲሁም መገበያየት ይችላል፡፡
6.11 የኩባንያው አክሲዮኖች በዕዳ መያዣነት
በሚሰጡበት ጊዜ ስለመያዣው ዝርዝር ሁኔታና ግዴታ በባለአክሲዮኖች ኤሌክትሮኒክስ መዝገብ ውስጥ ተገልጾ መያዝ ይኖርበታል፡፡
6.12 አንድ አክሲዮን በመያዣ ወይም በአላባ መብት የተሰጠ እንደሆነ በባለአክሲዮኑና
በመያዣ ወይም የአላባ መብት ተቀባይ መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር በባለአክሲዮኖች ጉባዔዎች ድምጽ የመስጠት መብት የሚኖረው
የመያዣ ወይም የአላባ መብት ተቀባዩ ነው፡፡
6.13 አግባብነት ያላቸው ሕጎችና መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም
ባለአክሲዮን በኩባንያው ያለውን አክሲዮን ያለገደብ ማስተላለፍ ይችላል፡፡
6.14
ታቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአክሲዮን ዝውውር በአክሲዮን መዝገብ ላይ ከተፃፈ በኋላ
አክሲዮን አስተላላፊው አክሲዮኑ
ከመመዝገቡ በፊት ያለውን የትርፍ ድርሻ ክፍፍል በተመለከተ የሚያነሳው የመብት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡
6.15
አግባብነት ያላቸው የአገሪቱ ሕጎች እንደተጠበቁ ሆኖ ባለአክሲዮኖች በካፒታል እድገትም ሆነ በሌላ ሁኔታ የሚወጡትን አዲስ
አክሲዮኖች ለመግዛት ባላቸው አክሲዮን መጠን የቀዳሚነት መብት አላቸው፡፡
6.16
እያንዳንዱ አክሲዮን ከአመት የትርፍ ድርሻ (ካለ) እንዲሁም
ማኅበሩ ሲፈርስ ከተጣራው ድርሻ የመካፈል መብት ያስገኛል፡፡
6.17 በህግ በተቃራኒው ካልተደነገገ
በስተቀር ማንኛውም ባለአክሲዮን በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ከባለአክሲዮንነት የሚመነጨውን መብት ሊያጣ አይችልም፡፡
6.18 ማናቸውም ባለአክሲዮን በስብሰባዎች የመሳተፍ፣ ድምጽ የመስጠት፣
የኩባንያውን ውሳኔ የመቃወም እንዲሁም ትርፍ የመካፈል መብት አለው፡፡
6.19 በህግ በተቃራኒው ካልተደነገገ በስተቀር እያንዳንዱ አክሲዮን
አንድ ድምጽ ያለው ሲሆን የድምጽ መስጠት መብትም በተፈረመው አክሲዮን መጠን ይሆናል፡፡
6.20 አግባብነት ባላቸው ሕጎችና መመሪያዎች መሰረት አክሲዮኑን በዋስትናት
የማስያዝ መብት ይኖረዋል፡፡
6.21 ማንኛውም ባለአክሲዮን በራሱ ወይም ሦስተኛ
ወገንን ወክሎ የጥቅም ግጭት በሚያስነሱ ጉዳዮች ላይ ድምጽ መስጠት አይችልም፡፡
6.22 ማናቸውም ባለአክሲዮን በማናቸውም ጊዜ ሰነዶችን የመመልከትና
የዳይሬክተሮችን ሪፖርትና የኩባንያውን የሂሣብ መዛግብት ቃለ-ጉባዔ እና በስብሰባ የተሳታፊዎችን ስም ዝርዝር ግልባጭ የማግኘት መብት
አለው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ባለአክሲዮኑ ሊከፍል የሚገባው የአገልግሎት ክፍያ በዳይሬክተሮች ቦርድ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ ሰባት
ትርፍ አከፋፈል
7.1 የኩባንያው ዓመታዊ ትርፍ ለባለአክሲዮኖች የሚከፋፈለው ባለአክሲዮኖቹ በትርፍ ክፍፍሉ
ወቅት ባላቸው የአክሲዮን መጠን ልክ ነው፡፡
7.2 የትርፍ ክፍፍሉ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ፣በመድን ስራ አዋጅ ቁጥር 746/2004፣ በዚህ
መመስረቻ ጽሑፍ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጎች መሰረት ተቀናሽ መሆን ያለባቸው ሂሣቦች ከተቀነሱ በኋላ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡
አንቀጽ ስምንት
የኩባንያው የአስተዳደር አካላት
8.1 የኩባንያው አስተዳደር አካላት የሚከተሉት ናቸው፡፡
8.1.1 የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ፣
8.1.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ፣
8.1.3 ዋና ስራ አስፈጻሚ፣እና
8.1.4 የማኅበር ፀሐፊ፣
8.1.5 ኦዲተሮች፣
8.2 ከላይ የተመለከቱት የኩባንያው የአስተዳደር አካላት ሥልጣንና
ተግባር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ፣ በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር746/2004፣ በመድን ሥራ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 1163/2012፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣቸው መመሪያዎችና በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ በተወሰነው መሰረት ይሆናል፡፡
አንቀጽ ዘጠኝ
የዳይሬክተሮች ቦርድ
9.1 የኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ ዘጠኝ አባላት ይኖሩታል፡፡ ማንኛውም
ሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመመሪያ ያወጣውን ዝርዝር መሥፈርት እስካሟላ ድረስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል መሆን ይችላል፡፡
9.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በባለአክሲዮኖች
ጠቅላላ ጉባዔ ይሾማሉ፡፡
9.3 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ለሦስት ዓመታት ብቻ እንዲያገለግሉ
የሚመረጡ ሲሆን፤ ለተጨማሪ ጊዜ ለማገልገል እንደገና ሊመረጡ ስለሚችሉበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ይወሰናል፡፡
9.4 እያንዳንዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በስማቸው ከተመዘገቡት
አክሲዮኖች ውስጥ 10 (አስር) አክሲዮኖች በዋስትና ማስያዝ ያለበት ሲሆን፤ እነዚህ አክሲዮኖች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በሥራቸው
ላይ እስከቆዩና ኃላፊነት ካለባቸው ይህን እስከሚያወራርዱ ድረስ በኩባንያው እጅ ተይዘው ይቆያሉ፡፡
9.5 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ
እንዲሁም በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የተወሰነና ከኩባንያው ወጪ የሚታሰብ ወርሃዊ የሥራ ዋጋ ሊከፈላቸው ይችላል፡፡
9.6 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ እና የኩባንያው መደበኛ ዓመታዊ
ጠቅላላ ጉባዔ በሚወስነው መሰረት ከኩባንያው የዓመቱ የተጣራ ትርፍ ላይ የተወሰነ ድርሻ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እንዲከፈላቸው
ሊወሰን ይችላል፡፡
9.7 የኩባንያው ማናቸውም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በባለአክሲዮኖች
ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ በማናቸውም ጊዜ ከሥልጣኑ ሊወገድ ይችላል፡፡
9.8 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በራሳቸው ወይም በሦስተኛ ወገኖች
ስም ከኩባንያው ጋር የውድድር ተግባር መሥራት አይችሉም፡፡
9.9 በኩባንያውና በዳይሬክተሮች ቦርድ መካከል በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ
የሚደረገው ስምምነት ሁሉ አስቀድሞ የዳይሬክተሮች ቦርድን ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡
9.10
ኩባንያው በዋናው መ/ቤቱ በኢትዮጵያ የንግድ
ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 306 እና 311 ስር የተደነገጉትን ያካተተ ዝርዝር በኤሌክትሮኒክስ መንገድ አደራጅቶ
ማስቀመጥ አለበት፡፡
9.11 የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አመዳደብ፣ ሥልጣንና
ተግባር፣ የአበል መጠን፣ ከሥልጣን መሻር፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሁኔታና ሥርዓቶች አግባብነት ባላቸው ሕጎች እና ጠቅላላ ጉባዔው በሚያሳልፈው
ውሳኔ መሰረት ይሆናል፡፡
9.12 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የራሳቸውን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት
ደንብ እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡
አንቀጽ አስር
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ተግባር
10.1 የዳይሬክተሮች ቦርድ በሕግ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍ እና በባለአክሲዮኖች
ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎች መሰረት የተሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ የዋና ስራ አስፈጻሚውን የቅጥር ሁኔታና ሌሎች ልዩ ልዩ አበሎችና
ጥቅማጥቅሞችንም ይወስናል፡፡
10.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ
የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል፡፡
10.2.1 የኩባንያውን ዋና ስራ አስፈጻሚ ይሾማል፣ ይሽራል፣ ሥልጣኑንና
ተግባሩን እንዲሁም ለሥራው ክፍያ ይወስናል፡፡
10.2.2 የዋና ስራ አስፈጻሚውን የቅጥር
ሁኔታና ሌሎች ልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማጥቅሞች ይወሰናል፡፡
10.2.3 ለኩባንያው ያበረከቱትን ልዩ አስተዋጽኦ
መሰረት ባደረገ ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች ሽልማት ወይም ስጦታ እንዲያገኙ ሊወስን ይችላል፡፡
10.2.4 የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚያቀርባቸውን ተጠሪነታቸው ለእርሱ
የሆኑ የኩባንያውን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ያጸድቃል፤ የሥራ ሁኔታዎችንም ይወስናል፡፡
10.2.5 የኩባንያውን ድርጅታዊ መዋቅር፣ የሰው ኃይል ፍላጎትና የኩባንያውን
የኦፕሬሽን፣ የአስተዳደርና የፋይናንስ መመሪያዎችን ያጸድቃል፤
10.2.6 የኩባንያውን አስተዳደር እና የስብሰባ መደበኛ ሰነዶች እንዲያዙ
ያደርጋል፤
10.2.7 ሕጉ በሚያዘው መሰረት የኩባንያውን የሂሣብ ሰነዶችና መዛግብት
እንዲያዙ ያደርጋል፤
10.2.8 የኩባንያውን ሂሣቦች በኩባንያው ኦዲተሮች እንዲመረመሩ ያደርጋል፡፡
ስለኩባንያው የሂሣብ መግለጫ ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች መደበኛ ስብሰባ ያቀርባል፤
10.2.9 የኩባንያው ሦስት አራተኛ ካፒታል የጠፋ እንደሆነ የኩባንያውን
ባለአክሲዮኖች መደበኛ ጉባዔ ሳይዘገይ ይጠራል፤
10.2.10 በሕግና በመመስረቻ ጽሑፉ መሰረት መያዝ ያለባቸውን መጠባበቂያ
ገንዘቦች እንዲደራጁ ያደርጋል፡፡
10.2.11
በኩባንያው ስም በዋስትናም ሆነ ያለ ዋስትና ገንዘብ መበደርና በኩባንያው ስም የብድር ስምምነት የሚፈረሙትን
ኃላፊዎች ይወክላል፡፡
10.2.12 የኩባንያውን ገንዘብ በሕግ በተፈቀዱ የኢንቨስትመንት ተግባራት
ላይ ያውላል፤
10.2.13 የኩባንያውን ሀብቶች መሸጥ፣መለወጥ፣ ማስተላለፍ፣ ኩባንያው ለመግዛት የሚፈልጋቸውን
ማናቸውንም የቋሚ ንብረት ግዥዎች መፈጸም፣ ኩባንያውን የፋይናንስና ሌሎች ሰነዶች ማረጋገጥ፣ የቋሚ ንብረቶች ስም ማዘዋወርን ጨምሮ
ሌሎች ህጋዊ ተግባራትን በኩባንያው ስም የሚያከናውኑ ኃላፊዎችን የዳይሬክተሮች ቦርዱ አስቀድሞ እየወሰነ ይወክላል፡፡
10.2.14 የተወሰነ ጊዜ ሲጠናቀቅ በገንዘብ ተመልሶ የሚከፈል ወይም የተወሰነው ጊዜ ሲጠናቀቅ ወደ
አክሲየን የሚለወጡ
የዕዳ ሰነዶችን
ያወጣል፤ ከዚያም ጋር የተያያዙትን ዋስትናዎች
ያፀድቃል፡፡
10.2.15 በኩባንያው ስም ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር የሚገኙ የጠለፋ
ዋስትና ድርጅቶች ጋር ይደራደራል፤ እንደአስፈላጊነቱ ይህንን ተግባር የሚያከናውኑ የኩባንያው ኃላፊዎችን ይወክላል፡፡
10.2.16 ሌሎች
በህግና በባለአክሲዮኖች ጉባዔዎች የተወሰኑትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
አንቀጽ
አስራ አንድ
የጥቅም ግጭት
11.1
ማንኛውም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ከኩባንያው ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ ከሚችሉ ሁኔታዎች ራሱን ማራቅ እንዲሁም በራሱ እና በኩባንያው መካከል የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ማንኛውንም ሁኔታ ለቦርዱ ማሳወቅ አለበት።
11.2
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የራሳቸውን ኃላፊነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በኩባንያው እና በራሳቸው ጥቅም መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግጭት በሚያስነሱ
ጉዳዮች ላይ ድምጽ መስጠት አይችሉም፡፡
አንቀጽ አስራ ሁለት
የዋና ስራ አስፈጻሚ ስልጣንና ተግባር፣
12.1 ኩባንያው በዳይሬክተሮች ቦርድ የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
የሚኖረው ሲሆን፤ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች እና ከኃላፊነት ስለመታገድ ዝርዝር ሁኔታዎች በመድን ስራዎች አዋጅ
ቁጥር 746/2004፣ የመድን ስራ/ማሻሻያ/አዋጅ ቁጥር 1163/2012 እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪዎች መሰረት የሚወሰን
ይሆናል፡፡
12.2 የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ በኩባንያው ዳይሬክተሮች ቦርድ
የሚወሰኑትንና የሚሰጠውን አጠቃላይ አመራር ተከትሎ የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
12.1.1 ኩባንያውን በአገር ውስጥና በውጭ አገራት፣ ከመንግስታዊና የግል
ድርጅቶች እንዲሁም ከሦስተኛ ወገኖች ጋር የሚያደርገውን የሥራ ግንኙነት ይወክላል፡፡
12.1.2 ከዳይሬክተሮች ቦርድ በሚሰጠው ውክልና መሰረት የኩባንያውን ሀብቶች
ይሸጣል፣ ይለውጣል፣ ያስተላልፋል፣ ኩባንያው ለመግዛት የሚፈልጋቸውን ማናቸውንም የቋሚ ንብረት ግዥዎች ይፈጽማል፣ ኩባንያውን የሚመለከቱ
ሰነዶች ያረጋግጣል፤የቋሚ ንብረቶችን የስም ማዘዋወር ጨምሮ ሌሎች ህጋዊ ተግባራትን በኩባንያው ስም ያከናውናል፤
12.1.3 ተጠሪነታቸው ለእርሱ የሆኑ የኩባንያውን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣
በመምረጥ ሹመታቸው በዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲጸድቅ ያቀርባል፣
12.1.4 ቦርዱ በሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና መመሪያዎች መሰረት የኩባንያውን
ሌሎች ሠራተኞች ይቀጥራል፤ ያሰናብታል፣
12.1.5 በዳይሬክተሮች ቦርድ በጸደቁ ዝርዝር የሥራ መመሪያዎች መሰረት
አስተዳደራዊ እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን እንዲሁም ስምምነቶችን ይፈርማል፡፡
12.1.6 ስለኩባንያው አጠቃላይ ሥራ እና የፋይናንስ እንቅስቃሴ በየጊዜው
ለዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርቶችን ያቀርባል፡፡
12.1.7 በኩባንያው ስም ወኪሎች፣ የህግ አማካሪዎች፣ ነገረፈጆች እና
ጠበቆች በመሾም የውክልና ሥልጣን ይሰጣል፡፡
12.1.8 በኩባንያው ስም የባንክ ሂሣቦችን በመፈረም ይከፍታል፤ የኩባንያውን
የዕለት ተዕለት ሥራዎችንም ይመራል፣ ይከታተላል፡፡
12.1.9 ከተሰጡት ሥልጣን ውስጥ በከፊልም ሆነ በሙሉ ለኩባንያው ሌሎች
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በውክልና ይሰጣል፡፡
12.1.10 የኩባንያውን በጀት፣ የሥራ እቅዶችና የሥራ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት
ለዳይሬክተሮች ቦርድ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም በሥራ ይተረጉማል፡፡
12.1.11 የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔዎችን በሥራ ላይ ያውላል፤ ከቦርድ
የሚሰጡትን ሌሎች ሥራዎችንም ያከናውናል፡፡
12.1.12 በንግድ ሕጉ አንቀጽ 341 ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
በሕግ መሰረት የሚጠየቁትን ሪፖርቶች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወይም ለሌሎች የሥልጣን አካላት በወቅቱ ያቀርባል፡፡
አንቀጽ አስራ ሦስት
የማኅበር ፀሐፊ ተግባርና ኃፊነት
13.1 የማኅበር ፀሐፊ ተጠሪነቱ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ይሆናል፡፡
13.2 የማኅበር ፀሐፊ በንግድ ሕግ አንቀጽ
341 ስር የተዘረዘሩትን፣ በኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በዳይሬክተሮች ቦርድ የሚሰጡትን ሕጋዊ ተግባራት ያከናውናል፡፡
አንቀጽ አስራ አራት
ኦዲተሮች
14.1 የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኩባንያውን ኦዲተሮች
ይሾማል፡፡ ይኸውም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀርቦ መጽደቅ አለበት፡፡ የተሾሙት ኦዲተሮችም ቢያንስ እስከሚቀጥለው የባለአክሲዮኖች
ስብሰባ ድረስ በሥራ ላይ መቆየት ይገባቸዋል፡፡ ይሁንና በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የተሾሙ ኦዲተሮች ለሦስት ተከታታይ ዓመት
እንዲያገለግሉ ጠቅላላ ጉባኤው ማጽደቅ ይችላል፡፡
14.2 የኩባንያው ኦዲተሮች ሥልጣንና ተግባር፣ ተጠያቂነት እንዲሁም
የአበል ክፍያ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ፣ በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ በዚህ መመስረቻ
ጽሑፍ፣ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በሚያሳልፈው ውሳኔ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጎች መሰረት ይሆናል፡፡
14.3 ኦዲተሮች ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ሁሉ የዓለም አቀፍ
የኦዲት መስፈርቶችን ባሟላ ሁኔታ ተግባራቸውን ያከናውናሉ፡፡ ይኸም የሪፖርት አቀራረብን፣ የንብረትና ዕዳ አተማመንን፣ እና የመሳሰሉትን
ሁሉ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
አንቀጽ አስራ አምስት
ኩባንያው የሚቆይበት ጊዜ
በባለአክሲዮኖች ጉባዔ በሌላ ሁኔታ
ካልተወሰነ በስተቀር ኩባንያው ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል፡፡
አንቀጽ አስራ ስድስት
ሪፖርቶች
ኩባንያው የሂሣብ እና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶቹን አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ሕጎች፣
በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣቸው መመሪያዎች መሰረት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤ሪፖርቶቹንም
ያሳትማል፡፡
አንቀጽ አስራ ሰባት
የባለአክሲዮኖች ጉባዔዎች
ባለአክሲዮኖች የሚያካሂዷቸው የተለያዩ ጉባዔዎች
ዓይነት፣ የስብሰባ ጥሪ ሁኔታ፣ የድምጽ ብልጫና ኮረም እንዲሁም የጉባዔዎችን ሥልጣን በተመለከተ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግና በዚህ
መመስረቻ ጽሑፍ በተወሰነው መሰረት ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
17.1 የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔዎች ጠቅላላ ወይም አስቸኳይ ናቸው፡፡
17.2 የጠቅላላ ጉባዔዎችን ለመጥራት የሚችሉት አካላትና የአጠራሩ ሁኔታ
በንግድ ህግ አንቀጽ 366 በተደነገገው አግባብ ይሆናል፡፡
17.3 የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ በንግድ ህግ አንቀጽ 367 የተደነገጉትን
በሚያሟላ ሁኔታ መጠራት የሚኖርበት ሲሆን፤ በተለይም በጋዜጣ ወይም በሪኮማንዴ ደብዳቤ ጥሪው ሊተላለፍ ይችላል፡፡
17.4 ለጠቅላላ ጉባዔ የሚዘጋጀው አጀንዳ በንግድ ሕጉ አንቀጽ
370/371 መሰረት ለባለአክሲዮኖቹ እንዲገለጽ መደረግ ይኖርበታል፡፡
17.5 በእያንዳንዱ ጉባዔ ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ላይ ስለመገኘታቸው
የሚያስረዳ የስም መመዝገቢያ መያዝ አለበት፡፡
17.6 ማናቸውም ጉባዔ በቦርዱ ሊቀመንበር፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ከሌለ
በምክትሉ ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን፤ሁለቱም በማይኖሩበት ጊዜ ከዳይሬክተሮች መካከል በሹመት
ቀደምትነት ያለው፣ ቀደምትነት ያለው በማይኖርበት ጊዜ ደግሞ ጠቅላላ ጉባዔው የወቅቱን ሊቀመንበር ይመርጣል፡፡
17.7 በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013
አንቀጽ 380 በተደነገገው መሰረት ጉባዔው ድምጽ ቆጣሪዎችን ይመርጣል፡፡
17.8 የጉባዔው ውይይትና ውሳኔ በጽሑፍ ከተመዘገበ
በኋላ በዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና በፀሐፊው ተፈርሞ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ይተላለፋል፡፡ ዝርዝር አካሄዱና አፈጻጸሙ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይሆናል፡፡
17.9 የስብሰባ ጥሪን ቀድሞ ለባለአክሲዮኖቹ ስለማሳወቅ በኢትዮጵያ
የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 370 በተደነገገው መሰረት የሆናል፡፡
አንቀጽ አስራ ስምንት
ስለመደበኛ ጉባዔ
18.1 የኩባንያው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኩባንያው የሂሣብ
ዓመት ካለቀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ በዳይሬክተሮች ቦርድ መጠራት አለበት፡፡
18.2 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው የኩባንያውን ሀብትና ዕዳ ሚዛን፣ የትርፍና
ኪሳራ ሂሣብ እንዲሁም የዳይሬክተሮችንና የኦዲተሮችን ሪፖርቶች መርምሮ ያጸድቃል ወይም ያልተቀበለው መሆኑን ያስታውቃል፡፡
18.3 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው ከዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበለትን የትርፍ
ክፍፍል ተመልክቶ ትርፍ ለባለአክሲዮኖች እንዲከፋፈል ይወስናል ወይም አግባብነት ያለውን ሌላ ውሳኔ ያሳልፋል፡፡
18.4 ኩባንያው የዕዳ ሰነዶችን እንዲያወጣ መፍቀድና ከዚያም ጋር በተያያዘ የሚሰጡትን
መያዣዎች ይወስናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ አክሲየን የሚለወጡ የዕዳ ሰነዶች
በሚወጡበት ወቅት የነባር ባለአክሲየኖች የቅድሚያ መብት
ቀሪ ይሆናል፡፡
18.5 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን እና ኦዲተሮችን
ይሾማል፤ ይሽራል፤ አበላቸውንም ይወስናል፡፡
18.6 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔው በሕግ የአስቸኳይ ጉባዔው ሥልጣን ከሆኑት
ውጭ በሌሎች ጉዳዮች ሁሉ ተወያይቶ ይወስናል፡፡
አንቀጽ አስራ ዘጠኝ
ለመደበኛ
ጉባዔ የሚያስፈልግ ምልዓተ-ጉባዔና የድምጽ ብልጫ
19.1 ለመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አስፈላጊው አነስተኛ የባለአክሲዮኖች
ቁጥር (ምልዓተ-ጉባዔ) ፡-
19.1.1 ለመጀመሪያው
ጥሪ ድምጽ ለመስጠት መብት ያላቸው አክሲዮኖች ቢያንስ ሩቡን (25%) የያዙ ባለአክሲዮኖች ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
19.1.2 በሁለተኛው
ጥሪ ድምጽ ለመስጠት መብት ያላቸው የአክሲዮኖች ቁጥር ምንም ያህል ቢሆን በጉባዔው በተገኙት ባለአክሲዮኖች የሚጸና ውሳኔ ለማሳለፍ
ይችላል፡፡
19.2 በመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ የሚያልፈው በተራ የድምጽ ብልጫ
ነው፡፡ ስለድምጽ ብልጫው አቆጣጠር ድምጽ ያልሰጡትም ሆነ ድምጽ ያልተጻፈባቸው የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ካሉ ከግምት ውስጥ አይገቡም፡፡
19.3 በምልዓተ-ጉባዔ አለመሟላት ምክንያት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ
ካልተቻለ ሁለተኛው የጉባዔ ጥሪ የሚደረገው የመጀመሪያው ጥሪ በተደረገበት ዓይነት እና የጊዜ ሁኔታ ነው፡፡
አንቀጽ ሃያ
ስለአስቸኳይ ጉባዔ
አስቸኳይ
ጉባዔው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
20.1
የኩባንያውን
መመስረቻ ጽሑፍ የማሻሻል፤
20.2
የማህበሩን
ዋና ገንዘብ የማሳደግ ወይም የመቀነስ፤
20.3
የማህበሩን
ዜግነት የመለወጥ፤
20.4
ማህበሩ እንዲፈርስ፤
ወደ ሌላ አይነት የንግድ ማህበር እንዲለወጥ፣እንዲከፋፈል ወይም እንዲዋሃድ የመወሰን፤
20.5
ሌሎች በህግ
በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲታዩ ተለይተው የተሰጡት ጉዳዮች የመወሰን፤
አንቀጽ ሃያ አንድ
ለአስቸኳይ ጉባዔ የሚያስልገው ምልዓተ-ጉባዔ እና የድምጽ ብልጫ
ለአስቸኳይ ጉባዔ ስለሚያስልገው አነስተኛ የባለአክሲዮኖች ቁጥር (ምልዓተ-ጉባዔ)፡-
21.1 ለመጀመሪያ ጥሪ ድምጽ ለመስጠት መብት ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ አንድ ሦስተኛ
(33.3%) የሚወክሉ ባለአክሲዮኖች ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
21.2 በሁለተኛው ጥሪ ድምጽ ለመስጠት መብት ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ አንድ አራተኛ
(25%) የሚወክሉ ባለአክሲዮኖች ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡
21.3 በሦስተኛው ጥሪ ድምጽ መስጠት መብት ያላቸው ባለአክሲዮኖች የሚወክሉት ዋና ገንዘብ
(ካፒታል) ግምት ውስጥ ሳይገባ በተገኙት ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው ጉባዔው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
21.4 በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ለማሳለፍ በሁለት ሦሰተኛ (66.6%) ድምጽ ያስፈልጋል፡፡
አንቀጽ ሃያ ሁለት
የኩባንያው የሂሣብ ዓመት
የኩባንያው የሂሣብ ዓመት እ.ኤ.አ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ
ነው፡፡
አንቀጽ ሃያ ሦስት
ስለኩባንያው ሂሣብ
23.1 ኩባንያው ሂሣቡን እና የሂሣብ መዛግብቱን በኢትዮጵያ የንግድ ህግ፣ በመድን ስራ አዋጅ
ቁጥር 746/2004፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችና ሌሎች አግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት መያዝ አለበት፡፡
23.2 ኩባንያው በመድን ስራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው
ሕጎች መሰረት መሰራቱን ለማወቅ የሚያስችሉትን የኩባንያው የሥራ እንቅስቃሴ እና ኩባንያው ያለውን የገንዘብ አቅም ግልጽ በሆነና
በትክክለኛ ሁኔታ ሊያስረዱ የሚችሉ መዛግብትን መያዝ አለበት፡፡
23.3 ኩባንያው በእያንዳንዱ የሂሣብ ዓመት መመዝገቢያ ላይ የንብረቱን፣ የሀብቱንና የእዳውን
ዝርዝር የሚያመላክቱ ሰነዶች ማዘጋጀት አለበት፡፡
23.4 የሂሣብ ሪፖርቱ የኩባንያውን የሀብት፣ የኪሣራና ትርፉን ሂሣብ የሚገልጽ ዝርዝር፤
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ኦዲተሮች በጠቅላላ የሚያገኙትን የሥራ ዋጋ የሚያመለክት ትክክለኛ መረጃ የያዘ ካለም ስለትርፍ አከፋፈልም
እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡
23.5 የኩባንያውን የሥራ ሁኔታ የሚያመለክቱና ለባለአክሲዮኖች ስብሰባ የሚቀርቡ ሪፖርቶች
ግልባጭ ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መተላለፍ አለበት፡፡
23.6 ኩባንያው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መጠባበቂያ ሂሣቦች መያዝ አለበት፡፡
23.6.1 በቅድሚያ ለተከፈለ አረቦን መጠባበቂያ፣
23.6.2 ያልተከፈሉ የካሳ ክፍያዎች፣
23.6.3 በመድን ውሉ መሰረት የክፍያ ግዴታን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ተፈጽመው ነገር ግን የክፍያ
ጥያቄ ገና ያልቀረበባቸው ጉዳዮች፣
23.6.4 ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በመመሪያ ለሚወስናቸው ተመሳሳይ ጉዳዮች፣
23.7 የኩባንያው የተጣራ ትርፍ የሚባለው የኩባንያው ጠቅላላ ወጭዎችና ሌሎች አገልግሎቶች፣
ግዙፋዊ ህልዎት የሌላቸው ሀብቶች፣ ሕጋዊ መጠባበቂያዎች፣ ክፍያዎች እና አበሎች ከተቀነሱ በኋላ የሚገኘው ቀሪ ገንዘብ ነው፡፡
አንቀጽ ሃያ አራት
ተፈጻሚ ሕጎች
በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ ያልተገለጹ ሌሎች ሁኔታዎች በሙሉ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ፣
በመድን ስራዎች አዋጅ ቁጥር 746/2004፣ በመድን ሥራ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 1163/2012፣ በባለአክሲዮኖች ጉባዔዎች በሚተላለፉ
ውሳኔዎች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣቸው መመሪያዎች መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሃያ አምስት
ስለኩባንያው መፍረስ
25.1 ስለኩባንያው መፍረስ በተመለከተ አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
25.2 ስለኩባንያው መፍረስ የተሾሙት ንብረት አጣሪዎች ተግባራቸውን አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ
ሕጎች መሰረት ማከናወን አለባቸው፡፡
አንቀጽ ሃያ ስድስት
የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻያ
የባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ
ጉባዔ ይህንን የመመሥረቻ ጽሑፍ በማንኛውም ጊዜ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡
አንቀጽ ሃያ ሰባት
የመሸጋገሪያ ድንጋጌ
27.1 ይህ የተሻሻለ የመመስረቻ ጽሑፍ በስራ ላይ ከመዋሉ
በፊት የተጀመሩ ማናቸውም ጉዳዮች በነባሩ መመስረቻ ጽሁፍ መሰረት ፍጻሜ ያገኛሉ፡
27.2 ይህ የመመስረቻ ጽሑፍ በሰነዶች ማረጋገጫና
ምዝገባ አገልግሎት ጸድቆ ስራ ላይ እስከሚውል ድረስ በተሻሩት መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተከናወኑ ተግባሮች ሁሉ
ህጋዊ ውጤታቸው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
አንቀጽ ሃያ ስምንት
የተሻሻለው መመሥረቻ ጽሑፍ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ የተሻሻለ
የመመስረቻ ጽሑፍ በባለአክሲዮኖች 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጸድቆ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተመዘገበ ጊዜ ጀምሮ በሥራ
ላይ ይውላል፡፡
የመመስረቻ ጽሑፍ መግለጫ
የቡና ኢንሹራንስ አ/ማኅበር የመመስረቻ ጽሑፍ መግለጫ
የቡና
ኢንሹራንስ አ/ማኅበር የመመስረቻ ጽሑፍ መግለጫ
የኩባንያው
ባለአክሲዮኖች ኅዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረጉት 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እ.ኤ.አ በ2004ዓ.ም በመሥራች አባላት የጸደቁትን
የማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ድንጋጌዎች በማሻሻልና በመመስረቻ ጽሑፉ ውስጥ በማጠቃለል በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ
አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 400(1) መሰረት በማጽደቅ በስራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ከመመስረቻ ጽሑፍ መጽደቅ በኋላ በማኅበሩ
የተደረጉ ለውጦችን በተለይም የተከፈለ ካፒታል መጠን ጭማሪን፤ ከካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሕግ ማዕቀፎች እና በአፈጻጸም የታዩ
ጉድለቶችን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ታሕሳስ 16 ቀን
2018 ለሚያደርጉት 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 400(1) መሰረት
ለማጸደቅ የማኅበሩን መመስረቻ ጽሑፍ እንደሚከተለው ተሻሽሎ ቀርቧል፡፡
የተሻሻሉ፣ የተሰረዙ አዲስ የገቡ የመመስረቻ ጽሑፍ ድንጋጌዎች፣
|
ተ.ቁ |
የቀድሞ/ነባሩ ድንጋጌ |
የተሰረዘ/የተሻሻለ/አዲስ የገባ ድንጋጌ |
ማሻሻያ ያስፈለገበት
መሰረታዊ ምክንያት |
|
01 |
አንቀጽ
ሦስት ስለባለአክሲዮኖች
እና የመስራቾች ጥቅም 3.1
የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስማቸው ከዚህ መመስረቻ ጽሑፍ ጋር
አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 641 የተዘረዘሩት ናቸው፡፡ |
አንቀጽ
ሦስት የባለአክሲዮኖች
ስም፣ ዜግነት፣ የተፈረመና የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ስም፣ አድራሻ፣ዜግነት፣ የተፈረመና የተከፈለ የአክሲዮን ብዛት ከዚህ መመስረቻ ጽሑፍ ጋር አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 712 የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
|
ከነባር ባለአክሲዮኖች በተደረገ የአክሲዮን ማስተላለፍ ምክንያት የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ቁጥር በመጨመሩ
በመመስረቻ ጽሑፉ ውስጥ ይህንኑ ማካተት ስላስፈለገ |
|
02 |
3.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የኩባንያው መስራች ባለአክሲዮኖች ማኅበሩ የተመሰረተበትን የመመስረቻ ጽሑፍ የፈረሙና በመስራች ጉባዔ በጸደቀው የመመስረቻ ጽሑፍ በተያያዘው ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 242 ስማቸው ተዘርዝሮ የሚገኙት
ሲሆኑ፤ ማኅበሩን በማቋቋም ሂደት ለሰጡት አገልግሎትና የገንዘብ ፍሰት በግንባር ቀደምትነት መታሰብ ስለነበረባቸው ከኢንሹራንስ
ማኅበሩ ከሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ 6% (ስድስት በመቶ) ባላቸው የማግኘት መብት በአክሲዮን ይዞታቸው መጠን ማኅበሩ ትርፍ
ማስመዝገብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በነበሩት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ተከፍሏቸው ተጠናቋል፡፡ |
|
የማኅበሩ መስራች ባለአክሲዮኖች በመስራችነታቸው ማግኘት የነበረባቸውን የተለየ ጥቅም ተከፍሏቸው ስለተጠናቀቀ
ከመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ ማካተቱ አስፈላጊ ባለመሆኑ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ |
|
03 |
4.2 በመድን ስራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 እና በማሻሻያ
አዋጅ ቁጥር 1163/2012 ድንጋጌዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች መሰረት የኩባንያውን የንግድ ዓላማዎች
በሚያግዙ እና በሚያጠናክሩ ተጓዳኝ በሆኑ ተግባራት ላይ መሳተፍ፡፡
|
4.2
አክሲዮኖችን፣ ቦንዶችን፣ የዕዳ ሰነዶችን ማውጣት እና መዋዋል፣
|
ከካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር
1248/2013 መውጣትን ተከትሎ በአገሪቱ በተፈጠረው አማራጭ የስራ እድሎች ላይ ኩባንያው ሊሳተፍ እንዲችል በመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ በማካተት ጠቅላላ ጉባኤውና ቦርዱ በሚወስኑት አግባብ
ወደ ስራው መግባት አስፈላጊ በመሆኑ የተካተተ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ የቀድሞው አንቀጽ 4.2 ወደ አንቀጽ 4.3 እንዲሸጋሸግ
ተደርጓል፡፡ |
|
04 |
5.
የኩባንያው የተፈረመ ካፒታል ብር 200,000,000 (ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር) ሲሆን፤ እስከ 5ኛው አስቸኳይ ጉባዔ ድረስ ብር 178,006,800 (አንድ መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ ተከፍሏል፡፡ |
6.1 የኩባንያው የተፈረመ እና የተከፈለ ካፒታል ብር 1,000,000,000 (አንድ ቢሊዮን ብር) ነው፡፡
|
የኩባንያው ተከፈለ ካፒታል በማደጉ ይኽንኑ በመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ በማካተት ለ3ኛ ወገኖች ማሳወቅ አስፈላጊና
ሕጋዊ ውጤት ያለው በመሆኑ
|
|
05 |
6.1 የኩባንያው እያንዳንዳቸው ብር 100 ዋጋ ላቸው በጠቅላላው ብር
2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) አክሲዮኖች ያለው ሲሆን፤ ሁሉም ደአክሲዮኖች እኩል ዋጋ ያላቸው፣
አንድ አይነት እና ልዩ መብት የማያስገኙ ተራ አክሲዮኖች ናቸው፡፡ |
6.1 ኩባንያው እያንዳንዳቸው ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ዋጋ ያላቸው በጠቅላላው 10,000,000 (አስር ሚሊዮን) አክሲዮኖች ያለው ሲሆን፣ ሁሉም አክሲዮኖች እኩል ዋጋ ያላቸው፣አንድ ዓይነት እና ልዩ መብት የማያስገኙ ተራ አክሲዮኖች ናቸው፡፡ |
በባለአክሲዮኖች 5ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩ ካፒታል እንዲያድግ የተደረገው አዲስ አክሲዮኖችን
በማውጣት ሲሆን፤ ሁሉም የወጡ አክሲዮኖችም የተከፈሉ በመሆኑ የኩባንያውን ካፒታል በተከፈለው የገንዘብ መጠን ማሻሻል አስፈላጊ ስለሆነ |
|
06 |
6.2 አክሲዮኖች የማይከፋፈሉ ናቸው፡፡ ሆኖም ብዙዎች ሰዎች
የአክሲዮን የጋራ ባለሀብት በሚሆኑበት ጊዜ የሁሉንም ባለአክሲዮኖች መብት የሚወክል ከመካከላቸው መወከል አለባቸው፡፡ የጋራ ባለሀብቶች
ከባለአክሲዮንነት ለሚመነጩ ግዴታዎች ሳይከፋፈል በአንድነትና በነጠላ ኃላፊዎች ናቸው፡፡ |
6.2 የኩባንያው ካፒታል መጨመር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማኅበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18፣
በኢፌዲሪ
የንግድ ሕግ
አንቀጽ 442 እና
አግባብነት
ባላቸው
የኢትዮጵያ
ካፒታል
ገበያ
ባለስልጣን
ሕጎች
መሠረት
ተፈፃሚ
ይደረጋል፡፡ |
ካፒታል መጨመር አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ እስከዛሬ መሟላት ከሚገባቸው የሕግ ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ በካፒታል
ገበያ አዋጅ ቁጥር 1247/2013 እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጡ መመሪያዎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላት ግዴታ ስለሆነ ይህንኑ
በመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ ማካተት በማስፈለጉ፤ የአንቀጽ 6.2 አዲስ ድንጋጌ መግባትን ተከትሎ ነባሩ አንቀጽ 6.2 ድንጋጌ ወደ አንቀጽ 6.3 እንዲሸጋሸግ
ተደርጓል፡፡ |
|
07 |
6.3 በኢትዮጵያ
የንግድ ህግ አዋጅ
ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 273 የተመለከቱትን
ዝርዝሮች ያካተተ የአክሲዮን
ምስክር ወረቀት ለእያንዳንዱ
ባለአክሲዮን በስሙ ተመዝግቦ
ይሰጣል፡፡ በሰርቲፊኬቱ ላይ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
ወይም አባል ይፈርሙበታል፡፡ |
6.4
ኩባንያው ሁሉንም አክሲዮኖች
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ግዑዝ አልባ በሆነ ኤሌክትሮኒክስ መንገድ ይይዛል፡፡
|
በንግድ ሕግ አንቀጽ
373 መሰረት የማኅበሩ
ባለአክሲዮኖች የአክስዮን ምስክር ወረቀት በስማቸው ይሰጣቸው የነበረው አሰራር በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1247/2013 እና ለህዝብ የሚሸጡ ሠነደ
ሙዓለ ንዋዮችን ግዑዝ አልባ ስለማድረግ በወጣው የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1047/2017 መሰረት በኤሌክትሮኒክ መንገድ ግዑዝ
አልባ ተደርገው እንዲያዙ በተደነገገው አግባብ የመመስረቻ ጽሑፉን
ከሕጉ ጋር በተናበበ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቀደም ሲል 6.3 የነበረው ድንጋጌ 6.4 ሆኖ ተሻሽሏል፡፡ |
|
08 |
6.4
ኩባንያው በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ
ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 274(2) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች መሰረት የሚወሰኑ ዝርዝሮችን ያካተተ የባለአክሲዮኖች
መዝገብ ማዘጋጀትና በዋናው መ/ቤት መያዝ አለበት፡፡
|
6.5 ኩባንያው በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሚያወጣቸው እና ሌሎች አግባብነት
ባላቸው ሕጐች የሚወሰኑ
ዝርዝሮችን ያካተተ የባለአክሲዮኖችን መዝገብ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ አደራጅቶ ይይዛል፤ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ
ንዋይ ግምጃ ቤት ያስመዘግባል፤ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግምጃ ቤት ጋር በመተባበር ወቅታዊ መረጃዎችን ያዘምናል፡፡
|
በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ
አዋጅ እና የአፈጻጸም መመሪያዎች መሰረት ግዑስ አልባ በሆነ መንገድ ሰነዶችን አደራጅቶ መያዝ፣ለማዕከላዊ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ
ግምጃ ቤት ማስመዝገብና ወቅታዊ የማድረግ ኩባንያውን ግዴታ ተሻሽሎ ተካትቶበት በአንቀጽ 6.5 ስር እንዲገባ ተደርጓል፡፡ |
|
09 |
|
6.6 በዚህ አንቀጽ
ንዑስ አንቀጽ 6(5) መሰረት የተደራጀው መዝገብ በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በመደበኛ
የሥራ ሰዓት ክፍት ሆኖ በባለአክሲኖችም ሆነ አግባብነት ያለው ሰው ያለ ክፍያ
እንዲመለከተው ይደረጋል፡፡ |
ከካፒታል ገበያ አዋጅ እና
የአፈጻጸም መመሪያ ድንጋጌዎች አግባብ በመመስረቻ ጽሑፉ ውስጥ
የገባ አዲስ ንዑስ አንቀጽ ነው፡፡ |
|
10 |
|
6.7
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6(5) ስር የተደራጀውን የመዝገቡን
ግልባጭ
ወይም
በአጭሩ
የተውጣጣ
ጽሑፍ ባለአክሲዮን ወይም ሌላ አግባብነት ያለው ሰው እንዲሰጠው
ሲጠይቅ
የተወሰነውን የአገልግሎት ክፍያ በመፈጸም ማግኘት ይችላል፡፡ |
በንግድ ሕጉ እና በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅና መመሪዎች መሰረት የባለአክሲዮን መረጃ ማግኘት መብትን
ለመረጋገጥ የገባ አዲስ ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
11 |
|
6.8
የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚካሄድበትን አግባብ አስመልክቶ በሌሎች ሕጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አክሲዮኑ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ
ግምጃ
ቤት መመዝገብ
አለበት፡፡ |
በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1047/2017 መሰረት የተካተተ አዲ ድንጋጌ
ነው፡፡ |
|
12 |
|
6.9
የዳይሬክተሮች ቦርድ በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተፈቀደውን የካፒታል ጭማሪ አግባብነት ያለውን ሕግና መመሪያ በመከተል ፈቃድ ባላቸው ባለሙያዎች አስጠንቶ አክሲዮኖች ከተፃፈባቸው ዋጋ በሚበልጥ ዋጋ እንዲወጡ እና ለሽያጭ የሚወጡበትን ዋጋ ይወስናል፡፡ |
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ ያልነበረ ሲሆን፤ ካፒታል ጭማሪ በሚደረግ ጊዜ ለአዲስ ባለአክሲዮኖች ሽያጭ
ለማከናወን መፈጸም ያለባቸውን መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች በመመስረቻ
ጽሑፉ ውስጥ መደንገጉ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን ስለሚያሟላ የገባ አዲስ ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
13 |
|
6.10
በኢንሹራንስ እና የካፒታል ገበያ ሕጐችና መመሪያዎች ወሰን ውስጥ እና በተገቢው
የተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ፈቃድ እና መስፈርቶች መሠረት የተለያዩ ዓይነት ሠነደ ሙዓለ
ንዋይን ማለትም አክሲዮን፤ ቦንድ፤ ተዛማጅ ሰነደ ሙዓለ
ንዋዮች ወይም እነዚህን የመሰሉ የተለያዩ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ማውጣትና
ለሽያጭ ማቅረብ፤ መሸጥና
መግዛት እንዲሁም መገበያየት
ይችላል፡፡ |
የካፒታል ገበያ አዋጅ በፈጠረው
አማራጭ እድል ኩባንያው አቅሙን ለማጠናከር እና ተጨማሪ ካፒታል
ማግኘት እንዲችል በሚስማማ መንገድ የገባ አዲስ ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
14 |
6.5
የኩባንያው አክሲዮኖች በዕዳ መያዣነት በሚሰጡበት ጊዜ የመያዣ ውሉ በኩባንያው የባለአክሲዮኖች መዝገብ ላይ መመዝገብ እና በአክሲዮን ምስክር ወረቀቱ ጀርባ ስለመያዣው ሁኔታ ተገልጾ በኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ እና እርሱ በወከለው ስራ አስፈጻሚ መፈረም ይኖርበታል፡፡ |
6.11 የኩባንያው አክሲዮኖች በዕዳ
መያዣነት በሚሰጡበት ጊዜ
ስለመያዣው ዝርዝር ሁኔታና
ግዴታ በባለአክሲዮኖች ኤሌክትሮኒክስ
መዝገብ ውስጥ ተገልጾ
መያዝ ይኖርበታል፡፡
|
በተሻሻለው መመስረቻ ጽሑፍ በአንቀጽ 6.2 ስር አዲስ ድንጋጌ በመግባቱ እና ከአንቀጽ 6.4 እስከ
6.10 ድረስ አዲስ ድንጋጌዎች በመካተታቸው የነባሩ አንቀጽ 6.5 ከካፒታል ገበያ አዋጅና መመሪያዎች አንጻር ማሻሻያ ተደርጎበት
አንቀጽ 6.11 ሆኖ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት የነባሩ አንቀጽ 6.6 የተሻሻለው አንቀጽ 6.12 ሆኗል፡፡ |
|
15 |
6.7 ባለአክሲዮኖች
በኩባንያው ያሏቸውን አክሲዮኖች ያለገደብ ለሦስተኛ ወገኖች ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ |
6.13
አግባብነት ያላቸው
ሕጎችና መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ባለአክሲዮን በኩባንያው ያለውን አክሲዮን ያለገደብ ማስተላለፍ ይችላል፡፡ |
ከፍ ሲል በተካተቱት አዲስ ንዑስ አናቅጽ ምክንያት የነባሩ አንቀጽ 6.7 ከካፒታል ገበያ አዋጅና የአፈጻጸም
መመሪያ አንጻር ማሻሻያ ተደርጎበት አንቀጽ 6.13 ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡
|
|
16 |
|
6.14 ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአክሲዮን ዝውውር በአክሲዮን መዝገብ ላይ ከተፃፈ በኋላ አክሲዮን አስተላላፊው አክሲዮኑ ከመመዝገቡ በፊት ያለውን የትርፍ ድርሻ ክፍፍል
በተመለከተ የሚያነሳው የመብት
ጥያቄ ተቀባይነት
የለውም፡ |
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ያልነበረ
እና ከአክሲዮን ዝውውር አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በተግባር ካጋጠሙ ችግሮቶች በመነሳት የተካተተ አዲስ ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
17 |
6.8 በካፒታል እድገትም ሆነ በሌላ ሁኔታ የሚወጡትን አዲስ አክሲዮኖች ለመግዛት ባላቸው አክሲዮን መጠን ባለአክሲዮኖች የቀዳሚነት መብት አላቸው፡፡
|
6.15 አግባብነት ያላቸው
የአገሪቱ
ሕጎች
እንደተጠበቁ
ሆኖ
ባለአክሲዮኖች በካፒታል እድገትም ሆነ በሌላ ሁኔታ የሚወጡትን አዲስ አክሲዮኖች ለመግዛት ባላቸው አክሲዮን መጠን የቀዳሚነት መብት አላቸው፡፡ |
አዲስ አክሲዮኖች በሚወጡበት ጊዜ የካፒታል ገበያ አዋጅ እና አፈጻጸም መመሪያዎች ያስቀመጧቸውን ቅድመ ሁኔታዎች
ባሟላ መንገድ ነባር ባለአክሲዮኖች ቀዳሚነት መብት ያላቸው መሆኑን ባስቀመጠ መንገድ የነባሩ አንቀጽ 6.8 ድንጋጌ ማሻሻያ ተደርጎበት
አንቀጽ 6.15 ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡ በተመሳሳይ በነባሩ ከአንቀጽ 6.9 እስከ 6.12 የነበሩት ድንጋጌዎች እንደቅደም ተከተላቸው
ከአንቀጽ 6.16 እስከ 6.19 ሆነው ተሸጋሽገዋል፡፡ |
|
18 |
|
6.20 አግባብነት ባላቸው ሕጎችና መመሪያዎች መሰረት
አክሲዮኑን በዋስትና የማስያዝ መብት ይኖረዋል፡፡
|
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ
ያልነበረ አዲስ የገባ ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
19 |
|
6.21
ማንኛውም ባለአክሲዮን በራሱ ወይም ሦስተኛ
ወገንን ወክሎ የጥቅም ግጭት በሚያስነሱ ጉዳዮች ላይ ድምጽ መስጠት አይችልም፡፡
|
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ያልነበረ
እና ከጥቅም ግጭት ጋር በተገናኘ መካተት የሚገባው ስለሆነ አዲስ የገባ ድንጋጌ ነው፡፡ አንቀጽ 6.20 እና 6.21 አዲስ ድንጋጌዎች
በመጨመራቸው የነባሩ አንቀጽ 6.13 ድንጋጌ በተሻሻለው አንቀጽ 6.22 ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡ |
|
20 |
|
8.1.4
የማኅበር ፀሐፊ፣ |
በነባሩ ያልነበረ እና በንግድ ሕጉ መሰረት የኩባንያው አስተዳደር አካል ውስጥ መካተት ያለበት ስለሆነ የገባ
አዲስ ድንጋጌ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የነባሩ አንቀጽ 8.1.4 የነበረው በተሻሻለው አንቀጽ 8.1.5 ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡ |
|
21 |
9.2 የመጀመሪያዎቹ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በኩባንያው መመስረቻ
ጽሑፍ ላይ በመሥራች ጉባዔ አባላት የተሾሙት ሲሆኑ፤ በተከታታይ የሚሾሙት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ደግሞ በባለአክሲዮኖች
ጠቅላላ ጉባዔ ይሾማሉ፡፡ |
9.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ይሾማሉ፡፡ |
በነባሩ ውስጥ የመጀመሪዎቹ ዳይሬክተሮች ቦርድ ስለሚመረጡበት ሁኔታ ያስቀምጥ የነበረውን እንዲወጣ አድርጎ
ማሻሻል የተደረገበት ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
22 |
9.10 ኩባንያው በዋናው ጽ/ቤቱ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር
1243/2013 አንቀጽ 311 እና 306 ስር በተደነገገው የተጠቀሱትን ያካተተ ዝርዝር መዝገብ አደራጅቶ ማስቀመጥ አለበት፡፡ |
9.10
ኩባንያው በዋናው
መ/ቤቱ በኢትዮጵያ
የንግድ ህግ አዋጅ
ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 306 እና
311 ስር የተደነገጉትን ያካተተ
ዝርዝር በኤሌክትሮኒክስ መንገድ
አደራጅቶ ማስቀመጥ አለበት፡፡ |
በነባሩ አንቀጽ 9.10 ስር የነበረውን ከካፒታል ገበያ አዋጅ ማስፈጸሚ መመሪያ አንጻር በመስታረቅ የተሻሻለ
ድንጋጌ ነው፡፡ |
|
23 |
10.2.9
በኩባንያው ስም በዋስትናም ሆነ ያለ ዋስትና ገንዘብ መበደርና በኩባንያው ስም የብድር ስምምነት የሚፈረሙትን ኃላፊዎች ይወክላል፤ የዋና ስራ አስፈጻሚው የቅጥር
ሁኔታና ሌሎች
ልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማጥቅሞች
በዳይሬክተሮች ቦርድ
ይወሰናል፡፡ |
10.2.2
የዋና ስራ አስፈጻሚውን የቅጥር ሁኔታና ሌሎች ልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማጥቅሞች ይወሰናል፡፡
|
በነባሩ አንጽ 10.2.9 ስር ከሌላ ጽንሰ ሃሳብ ጋር ተዳምሮ የነበረውን ድንጋጌ በመለየት ራሱን ችሎ አንቀጽ
10.2.2 ሆኖ እንዲቀመጥ የተደረገ ማሻሻያ ነው፡፡ |
|
24 |
|
10.2.3
ለኩባንያው ያበረከቱትን ልዩ አስተዋጽኦ መሰረት ባደረገ ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ወይም ሠራተኞች ሽልማት ወይም ስጦታ እንዲያገኙ ሊወስን ይችላል፡፡ |
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ያልተካተተ እና በተግባራዊ አፈጻጸም ከገጠመ ክፍተት በመነሳት አንቀጽ 10.2.3
ሆኖ እንዲገባ የተደረገ አዲስ ድንጋጌ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ ከአንቀጽ 10.2.2 እስከ
10.2.8 የነበሩት ድንጋጌዎች እንደቅደም ተከተላቸው ከአንቀጽ 10.2.4 እስከ 10.2.10 ሆነው ተሸጋሽጓል፡፡ |
|
25 |
10.2.9
በኩባንያው ስም በዋስትናም ሆነ ያለ ዋስትና ገንዘብ መበደርና በኩባንያው ስም የብድር ስምምነት የሚፈረሙትን ኃላፊዎች ይወክላል፤ የዋና ስራ አስፈጻሚው የቅጥር ሁኔታና ሌሎች ልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማጥቅሞች በዳይሬክተሮች ቦርድ ይወሰናል፡፡ |
10.2.11 በኩባንያው ስም
በዋስትናም ሆነ ያለ
ዋስትና ገንዘብ መበደርና
በኩባንያው ስም የብድር
ስምምነት የሚፈረሙትን ኃላፊዎች
ይወክላል፡፡
|
ከነባሩ አንቀጽ 10.2.9 ስር በነበረው ከፊል ሃሳብ በተሻሻለው አንቀጽ 10.2.2 ስር የገባ በመሆኑ የነባሩ አንቀጽ 10.2.9 የነበረው ቀሪ ድንጋጌ ሃሳብ አንቀጽ
10.2.11 ሆኖ ተሸጋሽጓል፡፡ በዚህም ምክንያት አንቀጽ 10.2.10 እና 10.2.11 የነበሩት አንቀጽ 10.2.12 እና
10.2.13 ሆነው ተሸጋሽገዋል፡፡ |
|
26 |
|
10.2.14
የተወሰነ ጊዜ ሲጠናቀቅ በገንዘብ
ተመልሶ የሚከፈል ወይም የተወሰነው
ጊዜ ሲጠናቀቅ ወደ አክሲዮን የሚለወጡ
የዕዳ ሰነዶችን
ያወጣል፤ ከዚህም ጋር የተያያዙትን ዋስትናዎች ያፀድቃል፡፡ |
የካፒታል ገበያ አዋጅ ይዞት
በመጣውን አዲስ አማራጭ መሰረት ኩባንያው ተጠቃሚ የሚሆንበትን
በመመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ ለማካተት የገባ አዲስ ድንጋጌ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት የነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 10.2.12
እና 10.2.13 በተሻሻለው አንቀጽ 10.2.15 እና 10.2.16 ሆነው ተሸጋሽገዋል፡፡ |
|
27 |
|
አንቀጽ አስራ አንድ የጥቅም ግጭት 11.1 ማንኛውም የዳይሬክተሮች
ቦርድ አባል ከኩባንያው ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ ከሚችሉ ሁኔታዎች ራሱን ማራቅ እንዲሁም በራሱ እና በኩባንያው መካከል የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ማንኛውንም ሁኔታ ለቦርዱ ማሳወቅ አለበት። 11.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የራሳቸውን ኃላፊነትና
ተጠያቂነት እንዲሁም በኩባንያው እና በራሳቸው ጥቅም መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግጭት በሚያስነሱ
ጉዳዮች ላይ ድምጽ መስጠት አይችሉም፡፡ |
ነባሩ መመስረቻ ጽሁፍ ውስጥ ያልነበረ የዳይሬከተሮች ቦርድ አባላትን የጥቅም ግጭት መርሆዎችን ማካተት አስፈላጊ
ስለሆነ የገባ አዲስ ድንጋጌ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በነባሩ አንቀጽ 11 ስር የነበሩት ድንጋጌዎች ከርዕሳቸው ጨምሮ አንቀጽ
12 ሆነው እንዲሸጋሸጉ ተደርጓል፡፡ |
|
28 |
11.3
ማኅበሩ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ተጠሪ የሆነ
የራሱ ፀሐፊ የሚኖረው ሲሆን፤ በንግድ ሕግ አንቀጽ 341 ስር የተዘረዘሩትን፣ በኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በዳይሬክተሮች
ቦርድ የሚሰጡትን ሕጋዊ ተግባራት የሚያከናውን ይሆናል፡፡
|
አንቀጽ
አስራ ሦስት የማኅበር
ፀሐፊ ተግባርና ኃፊነት 13.1
የማኅበር ፀሐፊ ተጠሪነቱ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ይሆናል፡፡ 13.2
የማኅበር ፀሐፊ በንግድ ሕግ አንቀጽ 341 ስር የተዘረዘሩትን፣ በኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚና በዳይሬክተሮች ቦርድ የሚሰጡትን ሕጋዊ ተግባራት ያከናውናል፡፡ |
በነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 11.3 ስር ከዋና ስራ አስፈጻሚ እና የማኅበር ፀሐፊ ስልጣንና ተግባር
በሚል በአንድ ላይ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን፤ የማኅበር ፀሐፊ በንግድ ሕጉ መሰረት አንድ የአስተዳደር አካል በመሆኑ ራሱን ችሎ
በአንድ አንቀጽ ስር እንዲካተት እና ዘርዘር ብሎ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአንቀጽ 12 እስከ 26 የነበሩት
አንቀጾች 227እንደቅደም ተከተላቸው ከአንቀጽ 14 እስከ 28 ድረስ እንዲሸጋሸጉ ተደርጓል፡፡ |
|
29 |
|
18.4
ኩባንያው የዕዳ
ሰነዶችን እንዲያወጣ መፍቀድና ከዚያም ጋር በተያያዘ የሚሰጡትን
መያዣዎች ይወስናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ አክሲየን የሚለወጡ የዕዳ ሰነዶች
በሚወጡበት ወቅት የነባር ባለአክሲየኖች የቅድሚያ መብት
ቀሪ ይሆናል፡፡
|
ከፍ ሲል በተጠቀሱት ምክንያቶች
የነባሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 16 በተሻሻለው ወደ አንቀጽ
18 የተሸጋሸገ ሲሆን፤ በነባሩ አንቀጽ 16.4 ስር በኢ/ካፒታል ገበያ አዋጅ በተፈቀደው መሰረት የሚወጡ የዕዳ ሰነዶችን እና
ለሚወጡ የዕዳ ሰነዶች መያዣዎችን የመወሰን ስልጣን የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሆን የሚደነግግ አዲስ ንዑስ አንቀጽ
18.4 ሆኖ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት የነባሩ አንቀጽ 16.4 እና 16.5 እንደቅደም ተከተላቸው አንቀጽ
18.5 እና 18.6 ሆነው ተሸጋሽገዋል፡፡ |
|
30 |
አንቀጽ አስራ ስምንት ስለአስቸኳይ ጉባኤ የኩባንያው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡ 18.1
የኩባንያውን መመስረቻ ጽሑፍ ያሻሽላል፡፡ 18.2
አግባብነት ያላቸውን ሕጎችና መመሪያዎች በመከተል የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተጠንቶ በሚቀርበው ሃሳብ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ 18.3
የኩባንያውን ዜግነት ስለመለወጥ ወይም ኩባንያው እንዲፈርስ ለመወሰን በሚቀርብ ሃሳብ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ |
አንቀጽ
ሃያ ስለአስቸኳይ
ጉባዔ አስቸኳይ ጉባዔው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡ 20.1 የኩባንያውን መመስረቻ ጽሑፍ የማሻሻል፤ 20.2 የማህበሩን ዋና ገንዘብ የማሳደግ ወይም የመቀነስ፤ 20.3 የማህበሩን ዜግነት የመለወጥ፤ 20.4 ማህበሩ እንዲፈርስ፤ ወደ ሌላ አይነት የንግድ ማህበር እንዲለወጥ፣እንዲከፋፈል ወይም እንዲዋሃድ የመወሰን፤ 20.5 ሌሎች በህግ በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲታዩ ተለይተው የተሰጡት ጉዳዮች የመወሰን፤ |
በነባሩ አንቀጽ 18 ስር የተቀመጡት የባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጉባኤ ስልጣንና ተግባር ጥቅል የነበሩ ሲሆን፤
ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 400 አንጻር በመፈተሽ ሙሉ ለሙሉ ተዘርዝረው በአንቀጽ 20 ስር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ |
|
31 |
አንቀጽ ሃያ የኩባንያው የሂሣብ ዓመት የኩባንያው የሂሣብ ዓመት እ.ኤ.አ ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ነው፡፡ ሆኖም የኩባንያው የመጀመሪያ የሂሣብ ዓመት ኩባንያው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በዚያው ዓመት እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሆናል፡፡ |
አንቀጽ ሃያ ሁለት የኩባንያው የሂሣብ ዓመት ሆኖም የኩባንያው የመጀመሪያ የሂሣብ ዓመት ኩባንያው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በዚያው ዓመት እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሆናል፡፡ |
በነባሩ አንቀጽ 20 ስር
-----ሆኖም የኩባንያው የመጀመሪያ የሒሳብ ዓመት ኩባንያው ስራ
ከጀመረበት ቀን ጀምሮ በዚያው ኣመት እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሆናል በሚል የተቀመጠው በምስረታ ላይ ላለ
ኩባንያ ብቻ የሚያገለግል ድንጋጌ ስለሆነ ከተሻሻለው መመስረቻ ጽሑፍ ውስጥ በመሰረዝ ቀሪው ተሻሽሎ በአንቀጽ 22 ስር እንዲቀመጥ
ተደርጓል፡፡ |
|
32 |
አንቀጽ ሃያ አምስት የመሸጋገሪያ ድንጋጌ 25 ይህ የመመስረቻ ጽሑፍ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጄንሲ ጸድቆ ስራ ላይ እስከሚውል ድረስ በተሻሩት መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተከናወኑ ተግባሮች ሁሉ ህጋዊ ውጤታቸው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ |
አንቀጽ ሃያ ሰባት የመሸጋገሪያ ድንጋጌ 27.1 ይህ የተሻሻለ የመመስረቻ ጽሑፍ በስራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተጀመሩ ማናቸውም ጉዳዮች በነባሩ መመስረቻ
ጽሁፍ
መሰረት
ፍጻሜ
ያገኛሉ፡ 27.2 ይህ የመመስረቻ ጽሑፍ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጄንሲ ጸድቆ ስራ ላይ እስከሚውል ድረስ በተሻሩት መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የተከናወኑ ተግባሮች ሁሉ ህጋዊ ውጤታቸው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ |
በነባሩ አንቀጽ 24 25 ስር የነበረው ደንጋጌ የተወሰነ ማስተካከያ ተደርጎበት በተሻሻለው አንቀጽ
27.1 ሆኖ እንዲቀመጥ ከተደረገ በኋላ በንኡስ አንቀጽ 2 ስር ደግሞ በነባር መመስረቻ ጽሑፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤትን በተመለከተ
በማያሻማ መንገድ ማካተት በማስፈለጉ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ |
|
33 |
አንቀጽ ሃያ ስድስት ይህ የተሻሻለ የመመስረቻ ጽሑፍ በባለአክሲዮኖች 5ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ጸድቆ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተመዘገበ በኋላ ሥራ ላይ ይውላል፡፡ |
አንቀጽ ሃያ ስምንት ይህ የተሻሻለ የመመስረቻ ጽሑፍ በባለአክሲዮኖች 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጸድቆ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተመዘገበ ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል፡፡
|
በነባሩ አንቀጽ 26 ስር የነበረው የተሻሻለ መመስረቻ ጽሑፍ የሚጸናበት ጊዜ በ8ኛው አስቸኳይ ጉባኤ ጸድቆ
በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ከተመዘገበበት እለት ጀምሮ ስለመሆኑ ማሻሻያ ተደርጎበት በአንቀጽ 28 ስር እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡ |
Nominated Candidates
Shareholders' Nominated Candidates
ማረሚያ
ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም የወጣው ማስታወቂያ እንደገና ማስተካከያ ተደርጎበት የወጣ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ
ለቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የቡና ኢንሹራንስ
አ.ማ ባለአክሲዮኖች ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት 11ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አሁን በሥራ ላይ
ያለው ቦርድ የሥራ ዘመን ስለሚያበቃ አዲስ የቦርድ አባላት ለመምረጥ የባለአክሲዮኖች የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ መሰጠቱ
የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ መሠረት የወጣውን መመሪያና መስፈርት የሚያሟሉትን በመለየት ከዚህ በታች የተገለጹትን ለዕጩ የቦርድ አባልነት
ያቀረበ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች የተጠቆሙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች
1.
አቶ
ጥጋቡ ኃይለየሱስ ዘውዱ
2.
አቦል
ቡና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ (ወ/ሮ አፀደ ግርማይ)
3.
አቶ
ሳምሶን ሉልሰገድ እጅጉ
4.
ዶ/ር
ግርማ ኡማ ኃይለማርያም
5.
አቶ
ይበቃል ተፈራ ስዩም
6.
አቶ
ይህንዓለም አቅናው መሸሻ
ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑና ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች የተጠቆሙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች
1.
አቶ
በቃሉ አያሌው ውድነህ
2.
አቶ
ውበቱ አሰፋ ገበየሁ
3.
ወ/ሮ
አበበች ታምራት ጌታሁን
4.
አቶ
ደረጀ መኮንን ዘውዱ
5.
አቶ
ገብሩ አየሁብዙ አላምረው
6.
ወረታ
ኢንተርናሽናል ኃላ/የተ/የግል ማህበር (አቶ አዲሱ ጌትነት ታደሰ)
7.
ዝናር
ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግል ማህበር (አቶ ዳንኤል ሙሉዓለም)
8.
አቶ
ወንድሙ አበረ ገድፍ
9.
አቶ
ሹምዩ ሢሳይ ገብሩ
10.
አቶ
ለውጤ ጥሩሰው ታደለ
11.
አቶ
ክፍለዮሐንስ ይመር በላቸው
12.
አቶ
ደምሰው አባተ በለው
ተጠባባቂዎች
1.
አበረ
ምሕረቴ የተመኝ (ክ/ዶ/ር)
2.
አቶ
ዮሐንስ ጉልላት አስማረ
3.
ቡና
ባንክ አ.ማ
4.
አቶ
አብርሃም ስዩም ንጋቱ
ማሳሰቢያ፡-
አቶ በቃሉ አያሌው ውድነህ፣ አቶ ክፍለዮሐንስ ይመር በላቸው፣ አቶ ይበቃል ተፈራ ስዩም እና
ተጠባባቂ የሆኑት አበረ ምሕረቴ የተመኝ (የክ/ዶ/ር) ለ3ኛ
ተከታታይ ጊዜ በዕጩነት የቀረቡ መሆናቸውን እናሳውቃለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ
ሳር ቤት አፍሪካ ሕብረት ጀርባ
ስልክ
ቁጥር 011-4-70 30 34
Notice of Annual General Meeting
Annual General Meeting Notice
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ
Bunna Insurance S.C
የባለአክሲዮኖች 12ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
የስብሰባ ጥሪ
ለቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር
1243/2013 አንቀፅ 366(1) ፣367(1) እና 370፤ እንዲሁም በማህበሩ መመስረቻ
ጽሁፍ አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 16.1 እና አንቀጽ 18 መሰረት የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 12ኛ ዓመታዊ
መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታሕሳስ
16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2"00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ
አበባ ከተማ ኢንተርለግዠሪ (በቀድሞው ስሙ ኢንተርኮንቲኔንታል) ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ
ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. ማህበሩን
የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የኩባንያው ስም፡-
ቡና
ኢንሹራንስ አ.ማ
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ አይነት፡- በጠቅላላ እና በህይወት መድን ስራዎች የተሰማራ፤
1.3 የአክሲዮን
ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ(ካፒታል)፡- 1,000,000,000
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ
የተከፈለ ዋና ገንዘብ(ካፒታል)፡- 1,000,000,000
1.5 የአክሲዮን ማህበሩ
የምዝገባ ቁጥር፡- MM/AA/3/0022504/2005
1.6 የአክሲዮን
ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ
ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 438/ለ
1.7 የኩባንያው ድረ-ገጽ https፡//www.bunnainsurance.com
2. የባለአክሲዮኖች 12ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1 እ.ኤ.አ
በ2024/2025 ሂሳብ አመት በማህበሩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችና የአክሲዮን ሽያጮችን መቀበል፣
2.2 እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ አመትን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.3 እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ አመትን የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፤
2.4 እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ አመትን በተገኘ የተጣራ የትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን በሚመለከት ተወያይቶ መወሰን፤
2.5 እ.ኤ.አ የ2023/2024
የሂሳብ ሪፖርትን በIFRS 17 ቀይሮ ለመስራት በውጪ ኦዲተሮች በተጠየቀው ተጨማሪ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
2.6 እ.ኤ.አ የ2025/2026
ሂሳብ አመት ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን እና እ.ኤ.አ የ2024/2025 ሂሳብ አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከተጣራ የትርፍ
ድርሻ የሚታሰብ ክፍያን መወሰን፤
2.7 የዳይሬክተሮች ቦርድ
አስመራጭ ኮሚቴን ሪፖርት ማድመጥ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ
ማካሄድ፣
2.8 የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ
ማጽደቅ
3 የባለአክሲዮኖች 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
3.1 የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
3.2 የማሕበሩን ካፒታል
ማሳደግ በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፣
3.3 የማሕበሩን
የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል፣
3.4 የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ
ማጽደቅ
4 ማሳሰቢያ ፡-
4.1 በጉባኤው ላይ መገኘት
የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የዉክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ
ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሶስት ቀን በፊት አዲስ አበባ ሳር ቤት ከአፍሪካ ህብረት ጀርባ በሚገኘው
ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ለዚሁ
ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የዉክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የዉክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ
ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መወከል የሚችለው
አንድ ሰው ብቻ መሆኑን በአክብሮት ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
4.2 የአክሲዮን ማህበሩ
ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ(ፋይዳ) ወይም የታደሰ
መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናዉንና
ኮፒ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች
ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ(ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011-1-26-28-61ወይም 011-1-26-31-46 ይደውሉ
የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ
Download Image
Office Timing: Mon - Fri 8:00 AM - 5:00 PM Sat : 8:00 AM - 12:30 PM