Media Center



Post Date: 20 Jun 2025

Post Date: 04 Nov 2023

Post Date: 30 Aug 2022

Post Date: 11 Oct 2022

Post Date: 15 Oct 2023

Post Date: 27 Nov 2023

Post Date: 06 Sep 2022

Post Date: 25 Sep 2021

Post Date: 15 Jan 2021

Post Date: 11 Dec 2020

Post Date: 11 Dec 2020

Post Date: 02 Sep 2020

Post Date: 27 Feb 2019

Post Date: 05 Mar 2019

Post Date: 05 Mar 2019

Post Date: 05 Jul 2024

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር አዲስ አመራሮችን መረጠ

በኢትዮጵያ ብቸኛው የጠሰፋ መድን ሰጪ ኩባንያ በመሆን የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ጠሰፋ መድን አክሲዮን ማኅበር አዲስ የቦርድ ሊቀመንበርና ምክትል የቦርድ ሊቀንበር ሰየመ።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር አዲስ የቦርድ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር የሰየመው ከወራት በፊት ባካሄደው የዳይሬከተሮች ቦርድ ምርጫ የተመረጡ የቦርድ አባላት ሹመት በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፀደቀላቸው በኋላ ነው፡፡
ሹመታቸው በብሔራዊ ባንክ የፀደቀላቸው የቦርድ አባላትም ከትናንት በስቲያ ባደረጉት ስብሰባ የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ ዳኟቸው መሃሪ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሊቀመንበር አድርገው መርጠዋል።
በምክትል የቦርድ ሊቀመንበርነት እንዲያገለግሉ የተመረጡት ደግሞ በተለያዩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ሲያገለሉ የነበሩና የኩባንያውም በግለሰብ ደረጃ ባለአክሲዮን የሆኑት አቶ ዮናስ በላይ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የአጋር ማክሮ ፋይናንስ የዕድገትና ስትራቴጂ ኦፊሰር በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው:
አዲሱ የኩባንያው የቦርድ ሊቀመንበር ኃላፊነቱን የተረከቡት እስካሁን ኩባንያው በቦርድ አባልነት ሲያገለግሉ ከቆዩት የኅብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሠረት በዛብህ ነው፡፡
ወ/ሮ መሠረት በዛብህ የቦርድ ሊቀመንበርነታቸውን ቢለቁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ አባልነታቸውን ካፀደቀላቸው ስድስት ተመራጮች መካከል አንዷ በመሆናቸው የቦርድ አባል ሆነው የሚቀጥሉ መሆኑ ታውቋል።
የምክትል የቦርድ ሊቀመንበር ሀላፊነት ቦታው ክፍት እንደነበር የሚያመለከተው መረጃ ይህም የሆነበት ምክንያት ምክትል የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትና የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ የጠለፋ መድን ኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ በመሾማቸው ነገር፡፡
ሪፖርተር ባገኘው መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ አባል ሆነው እያገለገሉ ሹመታቸውን ካፀደቀላቸው ስድስት ተመራጮች ውስጥ ሦስቱ አዲስ ሲሆኑ ሦስቱ ዳሞ በነባሩ ቦርድ ውስጥ የነበሩ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸው እንዲፀድቅ ቀርበውለት የነበሩት የዘጠኝ ተመራጮችን ቢሆንም የሦስቱን ተመራጮች ሹመት ሳያፀድቀው ቀርቷል።
እንደ ምንጮች ገለጻ የሦስቱ ተመራጮች ሹመት ያልፀደቀው ሦስቱም ሁለት የምርጫ ዘመን ስላገለገሉ ለሦስተኛ ጊዜ ሲቀጥሉ አይችሉም በሚል ምክንያት ነው፡ በዚሁ ውሳኔ መሰረት በተጠባባቂነት ተይዘው የነበሩ ሦስት ተመራጮቸ ሹመታቸው ባልፀደቀላቸው ሶስት የቦርድ አባላት እንዲተኩ የሚደረግ ይሆናል ተብሏል፡፡ ተተኪዎቹ የቦርድ አባላት ቦርዱን ሲቀላቀሉ የሚችሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ሲያፀድቅ እንደሆነም ይኸው የምንጮቻችን መረጃ ያመለክታል፡፡
በብሔራዊ ባንክ ሹመታቸው የፀደቀላቸው ስድስቱ የቦርድ አባላት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ተወካይ አቶ በላይ ጎርፉ፣ የቡና ኢንሹራንስ ኩባንያ ተወካይ አቶ ዳኛቸው መሃሪ፣ አቶ ዮናስ በላይ፣ የንብ ኢንሹራንስ ተወካይ ወ/ሮ ዙፋን አበበ፣ ወ/ሮ መሠረት በዛብህና አቶ ቀልመሳ ኩራ ናቸው:
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማንበር ወደ 130 የሆኑ ባለአክሲዮኖች አሉት፡፡ ከነዚህ ባለአክሲዮኖች ነጥ 17ቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ናቸው:: ሰባት ባንኮችም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የተሊያዩ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሥራ ኃላፊዎች በግለሰብ ደረጃ ባለአክሲዮን በመሆን ተመዝግበዋል። በዚህ አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሠራተኞች ማኅበርም በባለአክሲዮንነት ተመዝግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ወቅት የተፈረሙ 2.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 2.4 ቢሊዮን ብሩ የተከፈለ ነው፡፡ ቀሪውም የተፈረሙ ካፒታል በዚህ ወር ወይም እስከ በጀት ዓቱ ማጠናቀቂያ ድረስ ተከፍሎ እንደሚያልቅ ይጠበቃል፡፡ የኩባንያው አገልግሎት እየሰፋ በመምጣቱ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ቀሪው የተፈረሙ ካፒታል ከተጠናቀቀ በኋላ አሁንም ካፒታሉን ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ ሪፖርተር